Ground Water Investigation and Development ሥልጠና ማጠናቀቂያ…!!!

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በሰው ሀይልና በማቴሪያል አደራጅቶ ወደ ስራ ከገባ ከ2008 ዓ.ም ጀምሮ በ20 መደበኛ የስልጠና ዘርፎች ከተለያዩ ክልሎችና የከተማ አስተዳደሮች ለተውጣጡ ከ3200 በላይ ለሆኑ የዘርፉ ባለሙያዎች፤አሰልጣኞችና ሰልጣኞች አጫጭር ተግባር ተኮር ሥልጠናዎችን የሰጠ ሲሆን፤ እስከ 2012 ዓ.ም በጀት ዓመት መጨረሻም የሰልጣኞቹን ቁጥር 4500 ለማድረስ እየሰራ ይገኛል፡፡

የ2012 ዓ.ም ዕቅድ አንድ አካል የሆነው ለ 1 ወር የቆየ በቲዎሪና በተግባር የተደገፈ የ Ground Water Investigation and Development ሥልጠና ከትግራይ፤ ከአፋር፤ ከቤኒሻንጉል ክልሎች እና ከድሬዳዋ አስተዳደር ለተውጣጡ ባለሙያዎች ተሰጥቷቸዋል፡፡

በሥልጠናው ማጠናቀቂያና ሰርተፊኬት አሰጣጥ ፕሮግራም ላይ የውሃ ቴክኖሎጂ ትምህርትና ሥልጠና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዓለማየሁ ጉደታ እንዲሁም አሰልጣኞችና የትምህርትና ስልጠና ባለሙያዎች ተገኝተዋል፡፡

ታህሳስ 27 ቀን 2012 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት