ump Operation and Maintenance የአሰልጣኞች ሥልጠና…!!!

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የውሃን ዘርፉ አቅም ግንባታ እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ባለፉት ዓመታት የሰው ሃብታችን ክህሎት ያለው፤ ከቴክኖሎጂ ጋር የተዋወቀ እንዲሁም በውሃው ዘርፍ ላይ እሴቶችን የሚጨምር ለማድረግ ከሚመለከታቸው የፌዴራልና የክልል ተቋማት ጋር በመቀናጀት እየሰራ ይገኛል፡፡

ኢንስቲትዩቱ ከውሃ ዘርፎች ውስጥ አንዱ በሆነው ኤሌክትሮመካኒካል ላይ በክልሎች ሥልጠና እየሰጡ በሚገኙ ፖሊቴክኒክ ኮሌጆች የሚገኙ አሰልጣኞችን ክፍተት በተግባር-ተኮር ሥልጠና በመሙላት የሚያሰለጥኑትን ስልጠና ጥራት እንዲያስጠብቁ የሚያስችል ስልጠና ሰጥቷል፡፡ ሥልጠናው ለ7 ቀናት የቆየ ሲሆን በቲዎሪ እና በተግባር የተደገፈ እንደሆነ በተቋሙ የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቴክኒካል ድጋፍና የብቃት ምዘና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የቴ/ሙ/ት/ስ ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ተስፋዬ ገልፀዋል፡፡

ታህሳስ 24 ቀን 2012 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ውኃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
የሕዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት