በውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሙያ የተሰጠ የብቃት ምዘና አገልግሎት…!!!

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት በ4 ዘርፎች የብቃት ምዘና ማዕከል አገልግሎት እንዲሰጥ ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርትና ሥልጠና ጥራት ሙያ ብቃትና ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን ዕውቅና ማግኘቱ ይታወቃል፡፡ ኢንስቲትዩቱ የውሃ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ተቋማትን ፍላጎት መሠረት በማድረግ የአቅም ግንባታ ድጋፎችን ከማከናወን ጎን ለጎን የብቃት ምዘና ማዕከል አገልግሎት በዘርፉ ለተሰማሩና ለሚሰማሩ ባለሙያዎች በመስጠት ለኢንስቲትዩቱ ተልዕኮ መሳካት ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል፡፡

በዚህ መሠረት የውሃ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፕሮግራም ድጋፍና የብቃት ምዘና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትምህርትና ሥልጠና ጥራት የሙያ ብቃት ምዘና ማረጋገጫ ባለስልጣን ጋር በመተባበር የካቲት 21 እና 22 ቀን 2012 ዓም በኢንስቲትዩቱ ግቢ ውስጥ ለዘርፉ ባለሙያዎች በውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሙያ በደረጃ ሁለት ለ11 ባለሙዎች የሙያ ብቃት ምዘና ሰጥቷል፡፡

በተግባርና በንድፈ-ሀሳብ የተዘጋጀውን ምዘና ከወሰዱ 11 ተመዛኞች ውስጥ አስሩ (10) የሚሆኑት በምዘናው ብቁ ሆነው ተገኝተዋል፡፡ በቀጣይም በውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሙያ በደረጃ ሶስት ምዘና ለመስጠት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች መጠናቀቀቃቸውን በኢንስቲትዩቱ የውሃ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ፕሮግራም ድጋፍና የብቃት ምዘና አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የብቃት ምዘና አገልግሎት ቡድን መሪ አቶ አስፋው ካሳ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የኢትዮጵያ ውሃ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (PRCD-27-6-12)